\”ናቢ ኬታ ሊቨርፑል እንደሚጫወት አውቃለው ፤ ይህ ግን ለእኛ ምንም የሚያመጣው ነገር የለም\” ሽመልስ በቀለ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አምበል ሽመልስ በቀለ ከነገው ጨዋታ በፊት ተከታዩን አጠር ያለ አስተያየት ሰጥቷል።

የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ 4 ሦስተኛ ጨዋታ ነገ ምሽት 5:30 በጊኒ እና ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድኖች መካከል በሞሮኮ ካዛብላንካ መሐመድ 5ኛ ስታዲየም የሚደረግ ሲሆን በጨዋታው ዋዜማም የዋልያዎቹ አሠልጣኝ ውበቱ አባተ የሰጡትን አስተያየት ከደቂቃዎች በፊት አቅርበን ነበር። አሁን ደግሞ የቡድኑ አምበል ሽመልስ በቀለ በስፍራው ለተገኙ የብዙሃን መገናኛ አባላት የሰጠውን አስተያየት ይዘን ቀርበናል።

\"\"

በቅድሚያ ሽመልስ እርሱ እና የቡድን አጋሮቹ ለጨዋታው ምን ያክል እንደተዘጋጁ ተጠይቆ \”ስብስባችን ጥሩ ሁኔታ ላይ ነው የሚገኘው ፤ በፊት ካለውም የበለጠ ጥሩ ስሜት ላይ ነው ያለው። እዚህ የመጣነው ነጥብ ለማግኘት ነው። ስለዚህ ሁሉም ተጫዋቾች ለዚህ ዝግጁ ናቸው። እኔም በግል በአሠልጣኝ ቡድኑ እና በአጋሮቼ ሙሉ ዕምነት አለኝ። ጥሩ ነገር ይጠብቀናል ብዬም አስባለው። በአጠቃላይ የነገውን ጨዋታ በጥሩ ሁኔታ እየተጠባበቅን እንገኛለን።\” በማለት ምላሽ ሰጥቷል።

በመቀጠል ደግሞ በጊኒ ብሔራዊ ቡድን ውስጥ ወሳኝ ተጫዋች ስለሆነው ናቢ ኬታ ተጠይቆ ይህንን ብሏል። \”ልክ ነው! ናቢ ኬታ ሊቨርፑል እንደሚጫወት አውቃለው ፤ ይህ ግን ለእኛ ምንም የሚያመጣነው የነገር የለም። ለማንም ምንም የተለየ ትኩረት አንሰጥም። የትም ቢጫወት ምንም አይመስለኝም። ከዚህ ቀደም እንደ ግብፅ፣ አይቮሪኮስት እና ጋና ያሉ ትልቅ ብሔራዊ ቡድኖችን ገጥመናል። ባለፈውም ግብፅን አሸንፈናል። የእሱ ሊቨርፑል መጫወት ምንም አይመስለንም።\”

\"\"