የነገውን የዋልያዎቹ ጨዋታ የሚመሩ ዳኞች ታውቀዋል

ነገ ምሽት 4 ሰዓት ኢትዮጵያ እና ጊኒ የሚያደርጉትን ተጠባቂ ጨዋታ ከቻድ የመጡ ዳኞች ይመሩታል።

በአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ማጣሪያ አራተኛ ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከጊኒ አቻው ጋር ነገ ምሽት 4 ሰዓት ፍልሚያውን ያደርጋል። ቡድኑ የመጀመሪያ ጨዋታው ካደረገበት ካዛብላንካ ከተማ ወደ ራባት የተጓዘ ሲሆን የጨዋታው ዳኞችም ከሀገራቸው ወደ ራባት መግባታቸው ታውቋል።

በዚህም ጨዋታውን ቻዳዊው የመሐል ዳኛ አልሀጂ አላኦ ማሀማት የሀገራቸው ልጆች ከሆኑት ረዳቶች ቦጎላ ኢሳ እና ኢሳ ያያ እንዲሁም አራተኛ ዳኛው ፖርሲ አርሚ አልፍሬድ ጋር በመሆን እንደሚመሩት ታውቋል። የጨዋታው ኮሚሽነር የሆኑት ረኔ ዊሊያምስ ደግሞ ከኮትዲቯር እንደመጡ ተመላክቷል።