ዋልያዎቹ ጊዜያዊ አሠልጣኞች አግኝተዋል

ከአሠልጣኝ ውበቱ አባተ ጋር የተለያየው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከፊቱ ያሉበትን ጨዋታዎች በማን እንደሚመራ ይፋ ሆኗል።

ያለፉትን 30 ወራት ገደማ በአሠልጣኝ ውበቱ አባተ ሲመራ የነበረው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሳምንታት በፊት ከአሠልጣኙ ጋር ከተለያየ በኋላ የሚሾመው አሠልጣኝ ሲጠበቅ የነበረ ሲሆን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽንም በቦታው ጊዜያዊ አሠልጣኞች መሾሙን ከደቂቃዎች በፊት ይፋ አድርጓል።
\"\"
በዚህም የፌዴሬሽኑ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ባደረገው ውይይት በቴክኒክ ዳይሬክተርነት እየሠሩ የሚገኙት ኢንስትራክተር ዳንኤል ገብረማርያም በጊዜያዊ ዋና አሰልጣኝነት ቀጣይ ጨዋታዎችን እንዲመሩ ከውሳኔ መድረሱን አስታውቋል።
\"\"
ኢንስትራክተር ዳንኤልን እንዲያግዙ በፕሪምየር ሊጉ በመስራት ላይ የሚገኙና በወቅታዊ ውጤታማነትም የተሻሉ ሆነው የተገኙት የባህር ዳር ከተማ አሰልጣኝ ደግአረገ ይግዛው ምክትል አሰልጣኝ ሆነው እንዲሰሩ ከውሳኔ የተደረሰ ሲሆን ፌዴሬሽኑ ለአሰልጣኙ እና ለክለባቸው ባህርዳር ከተማ ጥያቄ አቅርቦ ፈቃደኛ በመሆናቸው ምክትል አሰልጣኝ ሆነው መሾማቸው ተያይዞ ይፋ ሆኗል።