የሉሲዎቹ የአቋም መፈተሻ ጨዋታ ተሰርዟል

የኦሊምፒክ ማጣሪያ ጨዋታ የሚጠብቀው የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከሲሸልስ ጋር ሊያደርግ የነበረው የአቋም መፈተሻ ጨዋታ እንደማይከናወን ተገለፀ።
\"\"
በፓሪስ አዘጋጅነት ለሚከናወነው የ2024 የኦሊምፒክ ውድድር በአፍሪካ ዞን ማጣርያ ከቻድ ጋር የተደለደለው የኢትዮጵያ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ልምምዱን እያከናወነ እንደሚገኝ ይታወቃል።
\"\"
ቡድኑ ሰኔ 30 ከሲሸልስ አቻው ጋር የአቋም መለኪያ ጨዋታ እንደሚያደርግ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ከሁለት ቀናት በፊት ገልፆ የነበረ ቢሆንም የሲሸልስ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በገጠማቸው ችግር ጨዋታውን ማድረግ እንደማይችሉ በደብዳቤ ማሳወቃቸው አሁን ይፋ ሆኗል። በዚህም ሰኔ 30 ሊደረግ የነበረው ጨዋታ እንደማይከናወን ፌዴሬሽኑ አስታውቋል።