ከኢትዮጵያውያን ቤተሰብ የተገኘችው ተጫዋች ወደ ዓለም ዋንጫ ታመራለች

ናኦሚ ኃይሌ በዓለም ዋንጫ ተሳታፊ በሚሆነው የአሜሪካ ብሄራዊ ቡድን ውስጥ ተካተተች።

ከኢትዮጵያውያን ቤተሰቦች የተገኘችው ናኦሚ ኃይሌ ግርማ በዓለም ዋንጫ በሚሳተፈው የአሜሪካ ብሄራዊ ቡድን ስብስብ ውስጥ መካተቷ ታውቋል። ከዚህ በፊት በአሜሪካ ከ19፣ 17 እና 20 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድኖች ውስጥ ተሳትፎ የነበራት እና በ2020 የሀገሪቱ ምርጥ ወጣት ተጫዋች ክብር ያገኘችው ናኦሚ ለዋናው ብሄራዊ ቡድን አስራ ስድስት ጨዋታዎች አድርጋለች።
\"\"
ተጫዋቿ በዚህ ወቅት ለሳን ዲያጎ ዌቭ በመጫወት ላይ ስትገኝ ከአስደናቂው የውድድር ዓመት በኋላም ውጤታማው እና ከወዲሁ ለዋንጫ በታጨው ስብስብ ተካታ በዓለም ዋንጫው የምትሳተፍ ይሆናል።

ከአባትዋ አቶ ግርማ አወቀ እና ከእናትዋ ሰብለ ደምሴ በሳን ጆሴ ካሊፎርንያ የተወለደችው ናኦሚ በ2005 ማለዳ በተሰኘው የህፃናት ቡድን መጫወት ከጀመረች በኋላ በኮሌጅና በታዳጊ ቡድኖች ደረጃ ለበርካታ ክለቦች ተጫውታለች። በ2022 ደግሞ ለሦስት የውድድር ዓመታት ውጤታማ ጊዜ ካሳለፈችበት ስታንፎርድ ካርዲናል የተባለ የዩንቨርስቲ ቡድን ለቃ በትልቁ የአሜሪካ ሊግ ተሳታፊ ለሆነው ሳን ዲያጎ ዌቭ ፌርማዋን አኑራለች።
\"\"
በአውስትራሊያ እና በኒውዝላንድ በጣምራ የሚዘጋጀው የ2023 የዓለም ዋንጫ ከሁለት ቀናት በኋላ ይጀመራል።

ስለ ናኦሚ ግርማ የእግርኳስ ህይወት ከዓመታት በፊት ያዘጋጀነውን ፅሁፍ ተከታዩን ሊንክ በመጫን ይመልከቱ :- LINK