ሀድያ ሆሳዕና ረዳት አሰልጣኝ ቀጥሯል

ዮሐንስ ሳህሌን በዋና አሰልጣኝ የቀጠረው ሀድያ ሆሳዕና እያሱ መርሀፅድቅን በረዳትነት በድጋሚ ሾሟል።
\"\"

ከሳምንታት በፊት ዮሐንስ ሳህሌን ለቀጣዩ የ2016 የውድድር ዘመን ዋና አሰልጣኙ አድርጎ መቅጠሩን የነገርናችሁ ሀድያ ሆሳዕናዎች አሁን ደግሞ ከአሰልጣኙ ጋር በጋራ እንዲሰሩ ዶ/ር እያሱ መርሀፅድቅን ከሁለት ዓመት በኋላ ዳግመኛ የቡድኑ ረዳት አሰልጣኝ አድርጎ ሾሟል።
\"\"
የቀድሞው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፀሐፊ እንዲሁም በአሰልጣኝነት በድሬዳዋ ከተማ ፣ በሀድያ ሆሳዕና ፣ በጅማ አባጅፋር እና ያለፉትን ስድስት ወራት ደግሞ ከአሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ጋር በፋሲል ከነማ ረዳት ሆነው ካሳለፉ በኋላ ከዚህ ቀደም ወደአገለገሉበት ሀድያ ሆሳዕና ዳግም ተመልሰው የክለቡ ረዳት አሰልጣኝ ሆነው ተሹመዋል።