አንጋፋው አጥቂ ሳላዲን ሰዒድ ጫማውን ሰቅሏል

በተለያዩ ክለቦች እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ግልጋሎት የሰጠው ሳላዲን ሰዒድ ከእግርኳስ ራሱን አገለለ።
\"\"
ከአዲሱ ሚሌኒየም ወዲህ በኢትዮጵያ እግርኳስ ከታዩ ምርጥ አጥቂዎች መካከል አንዱ የሆነው ሳላዲን ሰዒድ ከስኬታማ የአስራ አምስት ዓመታት በላይ የእግርኳስ ህይወት ቆይታ በኋላ በዛሬው ዕለት ጫማውን መስቀሉን ለሶከር ኢትዮጵያ ገልጿል።
\"\"
በተለያዩ ክለቦች እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ግልጋሎት የሰጠው ሳላዲን ለእግርኳስ ቤተሰቡ ያለውን ምስጋና ያቀረበ ሲሆን ድረ-ገፃችንም ከእርሱ ጋር ያደረገችውን ቃለ መጠይቅ ከቆይታ በኋላ ይዛ የምትመለስ ይሆናል።