ኢትዮጵያ መድን ተከላካይ ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል

ቡድኑን እያጠናከረ የሚገኘው ኢትዮጵያ መድን የተከላካይ ስፍራ ተጫዋች የግሉ አድርጓል።
\"\"
በአሠልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ የሚመራው ኢትዮጵያ መድን በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አድጎ 3ኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁ ይታወሳል። በቀጣይ ዓመት የበለጠ ተጠናክሮ ለመቅረብ ሙሴ ከቤላ እና አቡበከር ወንድሙን ማስፈረሙን ገልፀን የነበረ ሲሆን በዛሬው ዕለት ደግሞ ሦስተኛ ተጫዋች ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል።

መድንን የተቀላቀለው ተጫዋች አዲስ ተስፋዬ ነው። የቀድሞ የወላይታ ድቻ፣ መከላከያ እና ሰበታ ከተማ ተጫዋች የነበረው ተከላካዩ ከ2014 ጀምሮ ለአዳማ ከተማ ግልጋሎት ሲሰጥ የነበረ ሲሆን አሁን ወደ ኢትዮጵያ መድን አምርቷል።
\"\"
በዝውውሩ በንቃት እየተሳተፈ የሚገኘው ኢትዮጵያ መድን በፌዴሬሽን ፊት ተጫዋች ማስፈረም ባለመቻሉ የተጫዋቾቹ ውል እየፀደቀ እንዳልሆነ ታውቋል።