ፈረሰኞቹ የሁለት ተጨማሪ ተጫዋቾችን ኮንትራት አራዝመዋል

በካፍ ቻምፒየንስ ሊግ ላይ የሚሳተፈው ቅዱስ ጊዮርጊስ የሁለት ተጫዋቾችን ውል ለተጨማሪ ዓመት አድሷል።
\"\"
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን ለተከታታይ ዓመታት ያሳካው እና በካፍ ቻምፒየንስ ሊግ ሀገራችንን የሚወክለው የወቅቱ የሊጉ ሻምፒዮን ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሰዓታት የናትናኤል ዘለቀን ኮንትራት አስቀድሞ ካራዘመ በኋላ አሁን ደግሞ የሁለት ተጫዋቾችን ውል አድሷል።
\"\"
ከወላይታ ድቻ ወጣት ቡድን እስከ ዋናው በመጣወት በኋላም ያለፉትን ሁለት ዓመታት ደግሞ በፈረሰኞቹ ቤት ቆይታ የነበረው የተከላካይ አማካዩ በረከት ወልዴ እና ከክለቡ ወጣት ቡድን የተገኘው የመሐል ተከላካዩ አማኑኤል ተርፉ የሁለት ተጨማሪ ዓመት ውልም በክለቡ ለመቆየት አኑረዋል።