ሊዲያ ታፈሰ እና ሦስት ኢትዮጵያዊያን ዳኞች ምሽት ወደ ታንዛኒያ ያመራሉ

በቅርቡ ራሷን ከዳኝነት ያገለለችው ሊዲያ ታፈሰ በኢንስትራክተርነት እንዲሁም ሦስት ኢትዮጵያዊያን አልቢትሮች በዳኝነት ግልጋሎት ለመስጠት ዛሬ አመሻሽ ወደ ዳሬ ሰላም ያቀናሉ።
\"\"
የሴካፋ ከ18 ዓመት በታች ሴቶች ዋንጫ ውድድር ከፊታችን ማክሰኞ ሐምሌ 18 ጀምሮ በታንዛኒያ አስናጋጅነት በዳሬ ሰላም ከተማ በይፋ ይጀመራል። ኢትዮጵያን ጨምሮ አምስት የቀጠናውን ሀገራት በሚያሳትፈው በዚህ ውድድር ላይ ሀገራችን ከተወከለችበት ብሔራዊ ቡድኗ በተጨማሪ አራት ኢትዮጵያዊያን በውድድሩ ላይ በተለያዩ ኃላፊነቶች ተመርጠው ዛሬ አመሻሽ ወደ ስፍራው እንደሚያቀኑ ሶከር ኢትዮጵያ የደረሳት መረጃ ያመላክታል።
\"\"
ከ20 ዓመታት የዳኝነት ህይወቷ በቅርቡ የተገለለችው እና ከወር በፊት በግብፅ ካይሮ የኢንስትራክተሮች ስልጠን ተካፍላ የነበረችው የቀድሞዋ ኢንተርናሽናል ዳኛ ሊዲያ ታፈሰ በአዲሱ ስራዋ ውድድሩን የዳኞት ከፍተኛ ኢንስትራክተር እና አሰሰር ሆና በመመረጧ ወደ ስፍራው ስታመራ ከእርሷ በተጨማሪም ሦስት ዕንስት ዓለም አቀፍ ዳኞችም ተመርጠዋል። በዚህም መሠረት መዳብ ወንድሙ እና ፀሀይነሽ አበበ በዋና ዳኝነት ወጋየሁ ዘውዴ በበኩሏ በረዳት ዳኝነት ለውድድሩ በመመረጣቸው ዛሬ አመሻሽ ወደ ስፍራው ያቀናሉ።