ኬኒያዊው አጥቂ የዛምቢያውን ክለብ ተቀላቅሏል

ከአርባምንጭ ከተማ ጋር ያለፉትን 2 ዓመታት ያሳለፈው ኬኒያዊው አጥቂው ወደ ዛምቢያ ሊግ አምርቷል።
\"\"
በ2014 የውድድር ዘመን ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ፕሪምየር ሊጋችንን ከተቀላቀሉ ተጫዋቾች መካከል የ27 ዓመቱ ኬኒያዊው አጥቂ ኤሪክ ካፓይቶ አንዱ ነው። በሀገሩ ክለብ ካሪዮ ባንጊ በነበረው የመጨረሻ ዓመት ቆይታ የኬኒያ ሊግ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ሆኖ የፈፀመው ተጫዋቹ በመቀጠል ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት አርባምንጭ ከተማን ባደገበት ዓመት በመቀላቀል ያለፉትን ሁለት የውድድር ዘመናት በክለቡ የቆየ ሲሆን ዘንድሮም ከክለቡ ጋር ያልተሳካ ዓመት አሳልፎ ወደ ዛምቢያ ሊግ አምርቷል።
\"\"

በተጠናቀቀው በዛምቢያ ሊግ ከ18 ክለቦች በደረጃ ሰንጠረዡ 13ኛ ላይ ተቀምጦ ያጠናቀቀውን ዛናኮ ክለብ ተጫዋቹን በአንድ ዓመት ውል አስፈርሟል።