ሴቶች ፕሪምየር ሊግ | ኢትዮ ኤሌክትሪክ ተጨማሪ ተጫዋቾችን አስፈርሟል

በአሰልጣኝ መሠረት ማኔ የሚመራው ኢትዮ ኤሌክትሪክ የተጨማሪ ተጫዋቾን ዝውውር አጠናቋል።
\"\"
በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ላይ ተካፋይ የሆነው ኢትዮ ኤሌክትሪክ በቀጣዩ ዓመት ተጠናክሮ ለመቅረብ ከቀናት በፊት አዳዲስ ተጫዋቾችን ሲያስፈርም ውላቸው የተጠናቀቁ ተጫዋቾችንም ውል ለተጨማሪ ዓመት ሲያራዝም እንደነበር ይታወሳል። በዛሬው ዕለት ደግሞ ክለቡ የሁለት ተጫዋቾችን ዝውውር ሲያጠናቅቅ የነባሮችን ውልም አድሷል።
\"\"
ነፃነት መና የክለቡ አዲሷ ፈራሚ ነች። ከወላይታ ድቻ ከተገኘች በኋላ ያለፉትን ረጅም ዓመታት በሀዋሳ ከተማ ቆይታን አድርጋ የህይወቷ ሦስተኛው ክለብ ኤሌክትሪክ ሆኗል። ምህረት ተሰማ የቡድኑ ሌላኛዋ አዲስ ፈራሚ ነች። በጌዲኦ ዲላ ፣ ንግድ ባንክ እና ያለፈውን ዓመት በአርባምንጭ ከተማ አሳልፋ ኢትዮ ኤሌክትሪክን ተቀላቅላለች።

\"\"

ክለቡ ከሁለቱ ፈራሚዎች በተጨማሪ የግብ ጠባቂዋ እየሩሳሌም ሎራቶ እና የአማካዩዋ ትዕግሥት ያደታን ውል አራዝሟል።