ዐፄዎቹ ተከላካይ ለማስፈረም ተስማሙ

አሰልጣኝ ውበቱ አባተን በይፋ ያስፈረሙት ፋሲል ከነማዎች አንድ ተከላካይ ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰዋል።

ከዚህ ቀደም በሊጉ ከነበራቸው ጥንካሬ ባሳለፍነው የውድድር ዓመት ተቀዛቅዘው የነበሩት ዐፄዎቹ በቀጣይ አመት የተሻለ ቡድን ለመገንባት አሰልጣኝ ውበቱ አባተን በመሾም የሁለት ተጫዋቾችን ዝውውር ማጠናቃቸው ይታወቃል። አሁን ደግሞ ተከላካዩ ምኞት ደበበን ለማስፈረም መስማማታቸውን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።
\"\"
ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጋር በአሜሪካ የሚገኘው ምኞት ወደ ሀገር ቤት ሲመለስ ዝውውሩን በይፋ እንደሚያጠናቅቅ ይጠበቃል። ተከላካዩ ከዚህ ቀደም በአርባምንጭ ከተማ፣ በደደቢት፣ በአዳማ ከተማ እና ሀዋሳ ከተማ የተጫወተ ሲሆን ያለፉትን ሁለት ዓመታት በፈረሰኞቹ ቤት ተከታታይ አመት የሊጉን ዋንጫ ማንሳቱ ይታወሳል።
\"\"
በተያያዘ ዜና ከዚህ በፊት ባጋራናቹ መረጃ የመስመር አጥቂው አማኑኤል ገብረሚካኤል ለዐፄዎቹ ለመጫወት መቃረቡን ጠቁመን እንደነበረ ይታወቃል።