አዳማ ከተማ አራተኛ ፈራሚውን አግኝቷል

የአሰልጣኝ ይታገሱ እንዳለው አዳማ ከተማ የተከላካይ መስመር ተጫዋች አስፈርሟል።
\"\"
በክለቡ የነበሩ ወሳኝ ተጫዋቾችን ለሌሎች ክለቦች አሳልፎ የሰጠው አዳማ ከተማ ምትክ የሚሆኑ አዳዲስ ተጫዋቾችን እያስፈረመ ይገኛል። አስቀድሞ አሸናፊ ኤልያስ ፣ ሱራፌል ዐወል እና ፍቅሩ አለማየሁን የስብስቡ አካል ያደረገው ክለቡ አሁን ደግሞ አራተኛ ፈራሚው በማድረግ ተከላካዩ መላኩ ኤልያስን አስፈርሟል።
\"\"
የቀድሞው የጋሞ ጨንቻ ተጫዋች የሆነው መላኩ ከ2011 ጀምሮ በአርባምንጭ ከተማ እስከተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ድረስ ሲጫወት ከቆየ በኋላ ቀጣዩ መዳረጋቸው አዳማ ሆኗል።