ሰመረ ሀፍታይ ከነብሮቹ ጋር ይቆያል

ሀዲያ ሆሳዕናዎች የመስመር አጥቂያቸውን ውል አድሰዋል።
\"\"
አሠልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌን በመንበሩ የሾመው ሀዲያ ሆሳዕና በዝውውሩ አዳዲስ ተጫዋቾችን እያስፈረመ የሚገኝ ሲሆን የነባር ተጫዋቾችንም ውል እያደሰ ይገኛል። በዛሬው ዕለትም የመስመር አጥቂው ሰመረ ሀፍታይን ውል ማራዘሙን ሶከር ኢትዮጵያ አውቃለች።
\"\"
ሰመረ ሀፍታይ ከሀድያ ጋር ለተጨማሪ ሁለት ዓመታት የሚያቆየውን ውል አራዝሟል። የእግር ኳስ ሂወቱ በወልዋሎ ዓ/ዩ ጀምሮ በራያ ዓዘቦ፣ መከላከያ እና በሀድያ ሆሳዕና መጫወት የቻለው ይህ ተጫዋች ስሙ ከተለያዩ የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች እየተያያዘ ቢቆይም በስተመጨረሻ ከቀድሞ አሰልጣኙ ዮሐንስ ሳህሌ ጋር ለሦስተኛ ጊዜ ለመስራት እና ከነብሮቹ ጋር ለመቆየት ውሉን አድሷል።