ዮሴፍ ዮሐንስ ወደ ቀድሞ ክለቡ ተመልሷል

የአማካይ መስመር ተጫዋቹ ዮሴፍ ዮሐንስ ወደ ቀድሞ ክለቡ የተመለሰበትን ዝውውር አገባዷል።
\"\"
በዝውውር መስኮት ወሳኝ የሆኑ ተጫዋቾችን እየቀላቀለ የሚገኘው የአሰልጣኝ ሥዩም ከበደው ሲዳማ ቡና ከአብዱራህማን ሙባረክ ፣ ደስታ ዮሐንስ ፣ ፍቅረየሱስ ተወልደብርሃን፣ ብርሀኑ በቀለ እና ጌታነህ ከበደ በመቀጠል ስድስተኛው ፈራሚ ዮሴፍ ዮሐንስ ሆኗል።
\"\"
ከሀዋሳ ከተማ ወጣት ቡድን ከተገኘ በኋላ በሲዳማ ቡና ፣ አዳማ ከተማ እና የተጠናቀቀውን የውድድር ዘመን ደግሞ በድሬዳዋ ያሳለፈው ተጫዋቹ ከሁለት ዓመታት በኋላ ወደ ቀደመ ክለቡ ሲዳማ በድጋሜ ተመልሷል።