ከፍተኛ ሊግ | ጋሞ ጨንቻ የቀድሞው አሰልጣኙን ቀጥሯል

የከፍተኛ ሊጉ ጋሞ ጨንቻ የቀድሞው አሰልጣኙ ማቲያስ ለማን ዳግም ቀጥሯል።

ያለፉትን ተከታታይ ዓመታት በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ላይ ጠንካራ ተፎካካሪ በመሆን የሚታወቀው ጋሞ ጨንቻ የተጠናቀቀውን ዓመት በምድብ አንድ አራተኛ ሆኖ የፈፀመ ሲሆን ለቀጣዩ የውድድር ዘመን ደግሞ በተሻለ ቁመና ላይ ሆኖ ለመገኘት ይረዳው ዘንድ የቀድሞው አሰልጣኙ ማቲያስ ለማን በዋና አሰልጣኝነት ቀጥሯል።

ረጅሙን የሥልጠና ዘመን ጋሞ ጨንቻን በማሰልጠን የሚታወቀው አሰልጣኙ ከ2014 ጀምሮ በፕሪምየር ሊጉ የአርባምንጭ ከተማ ረዳት አሰልጣኝ በመሆን ያገለገለ ሲሆን አሁን ደግሞ ወደ ቀድሞ ቤቱ በመመለስ ጋሞ ጨንቻን ተረክቧል።