ኢትዮጵያዊያን ዳኞች የዓለም ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታን ይመራሉ

አራት ኢትዮጵያን አለም አቀፍ ዳኞች ሞሮኮ ላይ የሚደረገውን የዓለም ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታን ይዳኛሉ።

የ2026 የዓለም ዋንጫ ጨዋታ በአሜሪካ ፣ ሜክሲኮ እና ካናዳ የጣምራ አዘጋጅነት ይከናወናል። በዚህ ውድድር ላይ ተካፋይ ለመሆን በአፍሪካ አህጉር የሚገኙ ሀገራት የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታዎችን ማድረግ የጀመሩ ሲሆን ዛሬ ሜዳዋ በካፍ መታገዱን ተከትሎ በሞሮኮዋ ኦጁዳ ከተማ በሚገኘው ስታድ ማኒሲፓል ስታዲየም ላይ በምድብ 9 የምትገኘዋ ቻድ ባለ ሜዳ በመሆን ማዳጋስካርን ምሽት 04:00 ላይ ስትገጥም አራት ኢትዮጵያውያን ኢንተርናሽናል ዳኞች ይህንን ጨዋታ በዳኝነት እንዲመሩት ስለ መመረጣቸው ሶከር ኢትዮጵያ ያገኘችው መረጃ አመላክቷል።

በመሐል ዳኝነት ጨዋታውን ቴዎድሮስ ምትኩ ሲመራው ፣ ትግል ግዛው እና ሙስጠፋ መኪ ረዳቶቹ ፣ በላይ ታደሰ በአንፃሩ አራተኛ ዳኛ በመሆን በጣምራ መርሐግብሩን ይመሩታል።