የዋልያዎቹን ጨዋታ የሚመሩ ዳኞች ታውቀዋል

ጋምቢያዊው ፖሊስ የኢትዮጵያ እና ቡርኪናፋሶን ጨዋታ እንዲመራ ታጭቷል።

ለቀጣዩ የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከቀናት በፊት ሞሮኮ ላይ የሶራሊዮን አቻውን በመግጠም የምድብ ፍልሚያውን የጀመረው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ነገ ደግሞ በሁለተኛ ግጥሚያው ከቡርኪናፋሶ ጋር ይገናኛል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከቡርኪናፋሶ ጋር ላለበት ለዚህ ጨዋታ ጋምብያውያን ዳኞች መመደባቸው ታውቋል። የጋምብያ ፖሊስ አባሉ ጃሜህ ለሚን በዋና ዳኝነት፣ ጃዎ አንዱልአዚዝና ዳርቦ ኦማር ደግሞ በረዳት ዳኝነት ጨዋታውን ሲመሩት ማላዊው ሀይዳራ ኢብራሂም በአራተኛ ዳኝነት እንዲሁም ዩጋንዳዊው አውዬ ዮሱፍ የጨዋታው ኮሚሽነር ሆነው ተመድበዋል።