በሴቶች ጥሎማለፍ ወደ ሩብ ፍጻሜ ያለፉ 4 ክለቦች ታውቀዋል

የኢትዮጵያ ሴቶች ጥሎማለፍ ውድድር 2ኛ ዙር ጨዋታዎች ትላንት ተደርገው ወደ ሩብ ፍጻሜ ያለፉት 4 ክለቦች ታውቀዋል፡፡

አበበ ቢቂላ ላይ በ08:00 አዳማ ከተማ ከ ቅድስት ማርያም ዩኒቨርሲቲ ያደረጉት ጨዋታ በአዳማ 3-1 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡ ቀጥሎ በተደረገው ጨዋታ ደግሞ ጌዲኦ ዲላ በአስገራሚ ጉዞው በመቀጠል ልደታ ክፍለ ከተማን 5-1 በማሸነፍ ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቅሏል፡፡

አአ ስታድየም ላይ በ09:00 ሊካሄድ የነበረው የድሬዳዋ ከተማ እና ኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርተት አካዳሚ ጨዋታ ድሬዳዋ በቦታው ባለመገኘቱ ምክንያት ሳይካሄድ ቀርቷል፡፡ ለአካዳሚም ፎርፌ ተሰጥቷል፡፡ ቀጥሎ በተካሄደው ጨዋታ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለከተማ ቦሌ ክፍለከተማን 1-0 በማሸነፍ ሌላው ሩብ ፍጻሜውን የተቀላቀለ ቡድን ሆኗል፡፡

የ2ኛው ዙር ቀጣይ ጨዋታዎች የካቲት 21 ተካሂደው ወደ ሩብ ፍጻሜው የሚያልፉ ክለቦች ይለያሉ፡፡

 

2ኛ ዙር

የካቲት 17 ቀን 2009

ድሬዳዋ ከተማ 0-3 ኢ.ወ.ስ. አካዳሚ (ፎርፌ)

ቦሌ 0-1 ንፋስ ስልክ ላፍቶ

አዳማ ከተማ 3-1 ቅድስት ማርያም

ልደታ 1-5 ጌዲኦ ዲላ

 

ማክሰኞ የካቲት 21 ቀን 2009

09:00 ጥረት ከ ኢትዮጵያ ቡና (አአ ስታድየም)

11:30 ደደቢት ከ ሲዳማ ቡና (አአ ስታድየም)

08:00 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ አርባምንጭ ከተማ (አበበ

ቢቂላ)

10: 00 መከላከያ ከ ሀዋሳ ከተማ (አበበ ቢቂላ)

ዳንኤል መስፍን

ዳንኤል መስፍን

ይህንን ፅሁፍ ያቀረብኩላችሁ ዳንኤል መስፍን ነኝ

ከፎቶው በታች ያለው የፌስቡክ ምልክት ተጭነው ሊያገኙኝ ይችላሉ
ዳንኤል መስፍን

ዳንኤል መስፍን

ይህንን ፅሁፍ ያቀረብኩላችሁ ዳንኤል መስፍን ነኝ ከፎቶው በታች ያለው የፌስቡክ ምልክት ተጭነው ሊያገኙኝ ይችላሉ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *