አመለ ሚልኪያስ ወደ መቐለ ከተማ አመራ  

መቐለ ከተማ የአጥቂ ስፍራ ተጫዋቹ አመለ ሚልኪያስን በአንድ አመት ኮንትራት የግሉ አድርጓል፡፡

አመለ ባለፈው የውድድር አመት ሀዋሳ ከተማን ለቆ ወደ ቀድሞ ክለቡ አርባምንጭ ከተማ ካመራ በኋላ በተለይ ዘንድሮ በመጀመርያው ዙር መልካም እንቅስቃሴ ማድረግ የቻለ ሲሆን ከክለቡ ጋር የነበረውን ኮንትራት ማጠናቀቁን ተከትሎ ማረፊያውን መቐለ ከተማ አድርጓል፡፡

መቐለ ከተማ በዝውውር መስኮቱ ተሳትፎ እያደረገ የሚገኝ ሲሆን እስካሁን ዱላ ሙላቱ ፣ ጫላ ድሪባ ፣ ሙሴ ዮሀንስ ፣ ታደለ ባይሳ ፣ አንተነህ ገብረክርስቶስ እና ዳንኤል አድሀኖምን ማስፈረም ችሏል፡፡

ዳንኤል መስፍን

ይህንን ፅሁፍ ያቀረብኩላችሁ ዳንኤል መስፍን ነኝ

ከፎቶው በታች ያለው የፌስቡክ ምልክት ተጭነው ሊያገኙኝ ይችላሉ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *