አሜ መሐመድ በይፋ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ፈረመ

ቅዱስ ጊዮርጊስ አጥቂው አሜ መሐመድን በዛሬው እለት በይፋ አስፈርሟል፡፡

ያለፉትን 3 የውድድር ዘመናት በጅማ አባ ቡና ያሳለፈው አሜ መሐመድ በክለቡ ቀሪ የአንድ አመት ኮንትራት የነበረው ቢሆንም ክለቡ የጠየቀውን ከፍተኛ የውል ማፍረሻ ገንዘብ በመክፈል መልቀቂያውን ተቀብሎ ለቻምፒዮኖቹ የሁለት አመት ፊርማውን አኑሯል፡፡

አሜ መሐመድ በሀገሪቱ ከሚገኙ ተስፈኛ አጥቂዎች አንዱ ሲሆን ጅማ አባ ቡና ወደ ፕሪምየር ሊጉ ባደገበት አመት የከፍተኛ ሊጉ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ ሆኖ አጠናቋል፡፡ በ20 አመት በታች እና ዋናው ብሔራዊ ቡድንም መጫወት ችሏል፡፡

በዝውውር መስኮቱ አስፈሪ እንቅስቃሴ እያደረጉ የሚገኙት ፈረሰኞቹ በመጪዎቹ ቀናትም ኢብራሂም ፎፋናን እንደሚያስፈርሙ ይጠበቃል፡፡ ኮትዲቯራዊው የመሰመር አጥቂ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ለመፈረም የተስማማ ሲሆን ከሀገሩ ሲመለስ በይፋ ይፈርማል ተብሏል፡፡

ቅዱስ ጊዮርጊስ በዚህ ክረምት አሜ መሐመድን ጨምሮ ጋዲሳ መብራቴ ፣ አብዱልከሪም መሐመድ ፣ ሙሉአለም መስፍን ፣ ታደለ መንገሻ እና ለአለም ብርሀኑን ሲያስፈርም የደጉ ደበበ ፣ አስቻለው ታመነ ፣ ሳላዲን በርጊቾ ፣ አበባው ቡታቆ ፣ ናትናኤል ዘለቀ እና በኃይሉ አሰፋን ውል ማራዘም ችሏል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *