የካፍ ፕሬዝደንት ለስራ ጉብኝት እሁድ አዲስ አበባ ይገባሉ

የካፍ ፕሬዝዳንት አህመድ አህመድ ለይፋዊ ጉብኝት የፊታችን እሁድ ምሽት አዲስ አበባ እንደሚገቡ ታውቋል።

ለሶስት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት ወደ አዲስ አበባ እንደሚመጡ የተነገረው ፕሬዝዳንቱ በጉብኝታቸውም ከኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒሰቴር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ጋር መንግስት በስፖርቱ ላይ ማድረግ ስላለበት ድጋፍ እንዲሁም ከኢፌድሪ ወጣቶች እና ስፖርት ሚኒሰቴር ሚንስትር አቶ ርስቱ ይርዳው ጋር ስለ ስፖርቱ እድገት ውይይቶችን ያደረጋሉ ተብሎ ያጠበቃል። አህመድ አህመድ በቆይታቸው በተለይ ከኢትዮጲያ እግር ኳስ ፌደሬሽን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ጋር ካፍ ከኢትዮጲያ ጋር ስላለው ግንኙነት እና የካፍ አካዳሚ የግንባታ ጉዳይ ብሎም ፌደሬሽኑ እየሰራቸው ስለለው ስራዎች ላይም እንደሚመክሩም ታውቋል።

በየካቲት ወር እዚው አዲስ አበባ ላይ የኢሳ አያቱን የ29 ዓመታት የአመራር መንበር የተረከቡት አህመድ ወደ ስልጣኑ ከመጡ በኃላ ብዙ ለውጦችን እያመጡ እንደሆነ ይታወቃል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *