የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በወዳጅነት ጨዋታ ሞሮኮን ይገጥማል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዚህ ሳምንት መጨረሻ የወዳጅነት ጨዋታ ለማድረግ ወደ ሞሮኮ  ያመራል፡፡ ቡድኑ ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ለቦትስዋና 51ኛ አመት የነፃነት በአል ምክንያት በማድረግ ወደ ጋቦሮኒ አቅንቶ የወድጅነት ጨዋታ አድርጎ 2ለ0 ተሸንፎ መመለሱ ይታወሳል፡፡

ቡድኑ በዚህ ሳምንት መጨረሻ ወደ ሞሮኮ ራባት አቅንቶ ጨዋታውን ለማድረግ በካፒታል ሆቴል መቀመጫውን በማድረግ በኢትዮጵያ ወጣቶች እና ስፖርት አካዳሚ ዝግጅቱን እያደረገ መሆኑ ሲገለፅ ጨዋታው የሚደረገው ከሞሮኮ የቻን ብሄራዊ ቡድን ጋር መሆኑን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን አስታውቋል፡፡ ሙሉ የትራንስፖርት እና የሆቴል ወጪ በሞሮኮ እግር ኳስ ፌደሬሽን እንደሚሸፈን የታወቀ ሲሆን የሞሮኮ ብሄራዊ ቡድን በ2018 በሚደረገው የቻን ውድድር ላይ እንደ መካፈሉ የወዳጅነት ጨዋታውን ለማድረግ መፈለጉ ተሰምቷል፡፡

የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በሚቀጥለው ሳምንት እንደሚደረግ የታወቀ ሲሆን በቦትስዋናው የወዳጅነት ጨዋታ ላይ የነበሩ ተጨዋቾች በዚህኛውም ጨዋታ ላይ እንደሚሳተፉ ለማወቅ ተችሏል፡፡

ሚካኤል ለገሰ

ሚካኤል ለገሰ

ይህንን ፅሁፍ ያቀረብኩላችሁ ሚካኤል ለገሰ ነኝ

ከፎቶው በታች ያለው የፌስቡክ እና ትዊተር ምልክትን ተጭነው ሊያገኙኝ ይችላሉ
ሚካኤል ለገሰ

ሚካኤል ለገሰ

ይህንን ፅሁፍ ያቀረብኩላችሁ ሚካኤል ለገሰ ነኝ ከፎቶው በታች ያለው የፌስቡክ እና ትዊተር ምልክትን ተጭነው ሊያገኙኝ ይችላሉ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *