አብርሀም መብራቱ ከአንድ ሳምንት በኋላ ወደ ሞሮኮ ያመራሉ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ እና የአሰልጣኞች ኢንስትራክተር አብርሀም መብራቱ ከአንድ ሳምንት በኋላ ለሚደረገው የኢንትራክተሮች ኢንስትራክተርነት ከፍተኛ ስልጠና ወደ ሞሮኮ ያመራሉ።

ካፍ ከአንድ ሳምንት በኃላ በሞሮኮዋ ዋና ከተማ ራባት ላይ ከአፍሪካ ለተወጣጡ 26 ኢንትስራክተሮች ስልጠና አዘጋጅቷል፡፡ ይህ ስልጠና የኢንተስራክተሮች ኢንተስትራክተር ለመሆን ያለመ ከፍተኛ ደረጃ ያለው የኤሊት ስልጠና ሲሆን ኢትዮጵያም በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ በዚህ ትልቅ ስልጠና ላይ በአሰልጣኝ እና ኢንተስራክተር አብርሀም መብራቱ ትወከላለች፡፡

የቀድሞው የፌስቡክ ገፃችን በኛ ቁጥጥር ስር የማይገኝ በመሆኑ አዲሱ ገፃችንን ሊንኩን በመከተል ላይ ያድርጉ – facebook.com/SoccerEthiopia

ካፍ ይህን ስልጠና ያዘጋጀው ከዚህ ቀደም የኢንተስራክተሮች ኢንስራክተር የነበሩ አብዛኛዎቹ በህይወት የሌሉ እና በእድሜ ምክንያት በዚህ ሙያ ላይ የማይገኙ በመሆናቸው እነሱን ለመተካት በማሰብ ይህ ስልጠና መዘጋጀቱ ተነግሯል፡፡ በዚህ ደረጃ እውቅ ከሚባሉት መካከል አንጋፋዎቹ ኢንስትራክተሮች ኦንቢንዴ እና ቤን ኮፊን እንዲተኩ እና በካፍ ውስጥ የስራ ዕድልን ለማግኘት ዕድል እንዳለውም ተገልጿል፡፡

በአሁኑ ሰዓት ለኦሊምፒክ ማጣሪያ ቡድናቸውን እያዘጋጁ የሚገኙት አሰልጣኙ ከማሊ ጨዋታ በኃላ ወደ ስፍራው የሚያመሩ ሲሆን ስልጠናውም  ከማርች 27 እስከ አፕሪል 3 ድረስም የሚቆይ ይሆናል፡፡ ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ ያደረጉት አሰልጣኙ “ይህን ትልቅ ስልጠና እድል በማግኘቴ ደስተኛ ነኝ። ለኔም ብቻ ሳይሆን ሀገሪቱን ወክዬ እንደመሳተፌ ልዩ ጥቅም አለው። ለሙያተኞቿ ተነሳሽነት ጉልህ አስተዋጽኦ ስላለው ደስ የሚል አጋጣሚ ነው።” ብለዋል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

error: