አዳማ ላይ ሊካሄድ የነበረው የሀዋሳ ከተማ እና ኢትዮጵያ ቡና ጨዋታ ወደ ሌላ ሜዳ ተሸጋገረ

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 26ኛ ሳምንት ሀዋሳ ከተማ ከ ኢትዮጵያ ቡና የሚያደርጉት ጨዋታ ሀዋሳ ከተማ አንድ የሜዳው ጨዋታ በገለልተኛ ሜዳ እንዲያከናውን በመቀጣቱ ምክንያት አዳማ ላይ ነገ ሊካሄድ መርሐ ግብር ወጥቶለት እንደነበር ይታወሳል።

ሆኖም የአዳማ ከተማ ፀጥታ አካላት ኃላፊነት አልወስድም በማለታቸው ጨዋታው ወደ አሰላ ስታዲየም እንደተሸጋገረ ለማወቅ ተችሏል። በዚህም ነገ 9:00 ላይ በአሰላ አረንጓዴ ስታድየም የሚከናወን ይሆናል።

ሀዋሳ ከተማ ወደ አሰላ ተጉዞ ጨዋታ ሲያደርግ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው። ከዚህ ቀደም ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ሊያደርገው የነበረው ጨዋታ በሀዋሳ በነበረው የፀጥታ ስጋት ወደ አረንጓዴው ስታዲየም ተዘዋውሮ 0-0 መለያየቱ የሚታወስ ነው።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

error: