የአሰልጣኞች አስተያየት | ሀዋሳ ከተማ 0-0 ኢትዮጵያ ቡና

ትላንት በዝናብ ተቋርጦ ዛሬ በቀጠለው ጨዋታ ሀዋሳ ከተማ ከ ኢትዮጵያ ቡና ያለ ግብ አቻ ከተለያዩ በኋላ የሁለቱ ቡድኖች አሰልጣኞች አስተያየት ሰጥተዋል።

አዲሴ ካሳ – ሀዋሳ ከተማ

በጣም አስቸጋሪ ጨዋታ ነበር። ምክንያቱም ትናንት አሠላ ላይ 45 ደቂቃ ተጫውተን ሞጆ ነው ያደርነው። አዳማ ነው የሚሆነው ተብለን ነበር። እንደገና ደግሞ እዚህ መጣን። ለተጫዋቾቸ በጣም ከባድ ነበር ቢሆንም ማድረግ የምንችለውን ለማድረግ ሞክረናል። በሜዳችን አለመጫወታችን ጎድቶናል። አንድ ጨዋታ ተጫውተን አንዱ ላይ ያልፋችኋል እንባላለን። ሁለት ሶስት ጨዋታዎች አሳልፈናል። አሁን ግን እንዳለቀ ነው የምናውቀው። ቀጣዮችን 4 ጨዋታዎች ሁለቱ በሜዳችን ነው። ከድሬ አለን፤ ከመከላከያ አለን። እንግዲህ ሁለቱ ላይ አቋማችን እናስተካክላለን ብዬ አስባለሁ። ምክንያቱም ሜዳችን ላይ ከተጫወትን ቆየን ከከተማችን ከወጣን 18 ቀናት በላይ ሆኖናል እና እነዚህ ነገሮች ትንሽ እየጎዱን ነው።

ገዛኸኝ ከተማ – ኢትዮጵያ ቡና

ጨዋታው እንደጠበቅነው አላገኝነውም። እኛ አስበን የመጣነው አዳማ ነበር፤ ከዛ ወደ አሰላ ተዘዋውሯል። ይሄ በዝግጅትም በሰነ-ልቦናም ጥሩ አይደለም። እንደገና ደግሞ ትናንት እንደዛ ዓይነት ሁኔታ ላይ አልፈን አዳማ ነው ተብለን እንደገና ደግሞ ማታ ላይ ወደ ቢሾፍቱ ተደርጓል። እንደዚህ አይነት ሁኔታዎች የሚያመጡት ተፅዕኖ ብዙ ናቸው። ስለዚህ እነዚህ ነገሮች ቢስተካከሉ፤ ከዛ ውጭ ያየነው ጥሩ እንቅስቃሴ ነው። በቀጣይ የተሻልን ሆነን እንቀርባለን ።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

error: