ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ| ፋሲል ከነማ ለመልሱ ጨዋታ ነገ ወደ ታንዛኒያ ያመራል

ዐፄዎቹ ለካፍ ኮንፌደሬሽን ዋንጫ የመልስ ጨዋታ ነገ ጠዋት ወደ ታንዛኒያ ያመራሉ።

ፋሲል ከነማዎች ባህር ዳር ኢንተርናሽናል ስታዲየም ላይ አዛምን በበዛብህ መለዮ ብቸኛ ግብ 1-0 ካሸነፉ በኋላ ለሁለት ቀናት እረፍት በማድረግ በአዲሱ አሰልጣኛቸው ሥዩም ከበደ እየተመሩ ባህር ዳር ላይ የሁለት ቀን ልምምድ አከናውዋል። በመቀጠልም የመልሱን ጨዋታ የሚያደርጉበት የሰው ሰራሽ ሜዳ ታሳቢ ባደረገ መልኩ ዝግጅት ለማድረግ ወደ አዲስ አበባ አምርተው አበበ ቢቂላ ስታድየም ላይ ለተከታታይ 5 ቀናት ልምምድ የሰሩ ሲሆን ቅዳሜ ለሚያደርጉት የመልስ ጨዋታም ነገ ጠዋት 3:00 ላይ ወደ ዳሬሠላም ይበራሉ።

ቡድኑ 18 ተጫዋቾችን ጨምሮ የአሰልጣኝ ቡድኑን እና ሌሎች አባላትን ይዞ ሲጓዝ በዛብህ መለዮ በህመም ከስብስቡ ውጪ በመሆኑ በፋሲል አስማማው ተተክቷል። በመጀመርያው ጨዋታ ተጎድቶ ተቀይሮ የወጣው ግብ ጠባቂው ሚኬል ሳማኬ በአንፃሩ ከጉዳቱ በማገገሙ ከተጓዦች መካከል መካተቱን ለማወቅ ተችሏል።

ወደ ዳሬሠላም የሚያመሩ 18 ተጫዋቾች

ግብ ጠባቂዎች፡ ሚኬል ሳማኬ፣ ጀማል ጣሰው

ተከላካዮች፡ ሰዒድ ሀሰን፣ ያሬድ ባዬ፣ ከድር ኩሊባሊ፣ አምሳሉ ጥላሁን፣ እንየው ካሳሁን፣ ሰለሞን ሀብቴ

አማካዮች፡ ሐብታሙ ተከስተ፣ ሱራፌል ዳኛቸው፣ ኪሩቤል ኃይሉ፣ መጣባቸው ሙሉ፣ ዓለምብርሀን ይግዛው፣ ዮሴፍ ዳሙዬ

አጥቂዎች፡ ኢዙ አዙካ፣ ሙጂብ ቃሲም፣ ሽመክት ጉግሳ፣ ፋሲል አስማማው


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡