ደቡብ ፖሊስ ፌዴሬሽኑ የማስተካከያ ዕርምጃ እንዲወስድ ጠየቀ

ፌዴሬሽኑ የሚወስናቸው እርስ በእርስ የሚጋጩ ውሳኔዎች በክለቡ ላይ የሞራል እና የገንዘብ ኪሳራ እያስከተሉ በመሆኑ ጉዳዩን በድጋሚ እንዲያጤን ደቡብ ፖሊስ ቅሬታውን አሰምቷል፡፡

ክለቡ በቅሬታው “የተጫዋች እና የአሰልጣኝ ቅጥርን የፈፀምነው ፕሪምየር ሊግ ተሳታፊ ናችሁ ስለተባልን ነው። አሁን ደግሞ ፕሪምየር ሊግ አትሳተፉም፤ በከፍተኛ ሊጉ ትሳተፋላችሁ መባሉ በክለባችን ላይ የሞራል እና የገንዘብ ኪሳራን አስከትሏል፡፡ ስለዚህም ፌዴሬሽኑ በአፋጣኝ ጉዳዩን ተመልክቶ የማስተካከያ ዕርምጃን እንዲወስድ” በማለት አቅርበዋል፡፡

ክለቡ ለፌዴሬሽኑ የላከው ደብዳቤ👇


© ሶከር ኢትዮጵያ

error: