መቐለ ከላውረንስ ላርቴ ጋር ሳይስማማ ሲቀር ከአንድ ተጫዋች ጋር ሊለያይ ተቃርቧል

ላውረንስ ላርቴ ለመቐለ ፊርማውን ሳይኖር ሲቀር የቡድኑ አማካይ ደግሞ መውጫው በር ላይ ቆሟል።

ባለፈው የውድድር ዓመት መከላከያን በመልቀቅ መቐለን በሁለት ዓመት ውል በመቀላቀል የአንድ ዓመት ቆይታ ያደረገው ሳሙኤል ሳሊሶ ቀሪ የአንድ ዓመት ውል እየቀረው ከምዓም አናብስት ጋር በስምምነት ለመለያየት ከጫፍ ደርሷል። ጉዳት አስተናግዶ ከሜዳ ከመራቁ በፊት ወሳኝ ግቦችን በማስቆጠር የቡድኑ ቁልፍ ተጫዋች መሆን ችሎ የነበረው ሳሙኤል በውድድር ዓመቱ ከሲዳማ ቡና ጋር በነበረው ጨዋታ ጉዳት ካስተናገደ በኃላ ነው ለረጅም ግዜ ከሜዳ የራቀው። ወደ ዓመቱ መገባደጃ ላይ ከጉዳት ተመልሶ ጨዋታዎችን በማድረግ የቻለ ሲሆን እስካሁን ድረስ ከቡድኑ ጋርም በይፋ አልተለያየም።

በሌላው ከመቐለ ጋር በተያያዘ ዜና ቡድኑን ለመቀላቀል ጫፍ ደርሶ የነበረው የጋናዊው የሃዋሳ ከተማ ተከላካይ ላውረንስ ላርቴ ዝውውር በመጨረሻ ሰዓት ሳይሳካ ቀርቷል። ቀደም ብሎ ክለቡን ለመቀላቀል ተስማምቶ የነበረው ይህ ተጫዋች በመጨረሻው ሰዓት ወደ ክለቡ ያልተዘዋወረበት ምክንያት ባይታወቅም ከሃዋሳ ከተማ ጋር ልምምድ መጀመሩን መመልከት ችለናል።


© ሶከር ኢትዮጵያ