የአአ እግርኳስ ፌዴሬሽን የኮሮና ቫይረስን ለመካለከል የሚረዳ የግማሽ ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ

የአአ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ በአሁኑ ወቅት በእጅጉኑ አሳሳቢ በሆነ ደረጃ የዓለም ህዝብ ስጋት የሆነውን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመካለከል ያቀረቡትን የድጋፍ ጥሪ በመቀበል የአዲስ አበባ እግርኳስ ፌዴሬሽን ሥራ አስፈፃሚ አባላት በወሰኑት ውሳኔ መሠረት በዛሬው ዕለት በከተማው አስተዳደር ፅህፈት ቤት በመገኘት የ500 ሺህ ብር ድጋፍ አድረገዋል።

ከህዝብ ጤና የሚበልጥ እና ቅድሚያ የሚሰጠው ምንም ነገር ባለመኖሩ ይህን የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉን የገለፀው ፌዴሬሽኑ በቀጣይ በሽታውን ለመቆጣጠር በሚደረገው ጥረት ከከተማው አስተዳደር ጎን በመቆም መሰል ድጋፎችን እንደሚያደርግ ለክቡር ከንቲባው በዛሬው ዕለት የገንዘብ ድጋፉን ባደረገበት ወቅት አሳውቋል።

ከከተማው እግርኳስ ፌዴሬሽን በተጨማሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና የተለያዩ ተጫዋቾች በተመሳሳይ ድጋፍ ማድረጋቸው ይታወቃል።

© ሶከር ኢትዮጵያ