ወልቂጤ ከተማ ስድስተኛ ተጫዋች አስፈርሟል

ዊልፍሬድ የሶህ የዝውውር መስኮቱ ከመዘጋቱ ቀደም ብሎ ለወልቂጤ ከተማ ፊርማውን ማኖሩ ታውቋል።

የ28 ዓመቱ አይቮሪኮስታዊ አጥቂ ዊልፍሬድ የሶህ ከዚህ ቀደም ከሀገሩ ክለቦች በተጨማሪ በኳታር እና ኢንዶኔዥያ ክለቦች የተጫወተ ሲሆን ለግብፁ ኤንፒ ክለብ መጫወቱ ፕሮፋይሉ ያሳያል። ጃኮ አራፋትን የለቀቀውና በአጥቂ ስፍራ ጥቂት አማራጮች የነበሩት ወልቂጤ ተጫዋቹን የዝውውር መስኮቱ ከመጠናቀቁ በፊት በማስፈረሙ ለሁለተኛው ዙር ውድድር አማራጩን እንደሚያሰፋለት ይጠበቃል።

ወልቂጤ በዚህ የዝውውር መስኮት ስድስት ተጫዋቾች አሰናብቶ በምትኩ ስድስት አዳዲስ ተጫዋቾች አስፈርሟል።

© ሶከር ኢትዮጵያ