ወልዋሎዎች ድጋፍ አድርገዋል

የወልዋሎ እግርኳስ ክለብ ለዓዲግራት የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ግብረ ኃይል የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ለደረሰው የኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝ ለመከላከል በርካታ ድጋፎች እየተደረጉ መቆየታቸው ይታወሳል አሁን ደግሞ የወልዋሎ ዓዲግራት ዩንቨርስቲ እግርኳስ ክለብ፣ የክለቡ የአሰልጣኞች ቡድን አባላት እና የፅህፈት ቤት ሰራተኞች በጋራ 165,000 (አንድ መቶ ስልሳ አምስት ሺህ ብር) ድጋፍ አድርገዋል።

ክለቡ ካደረገው ድጋፍ በተጨማሪም ደጋፊዎች በተናጠል እና በጋራ በመሆን በከተማው ድጋፍ እያደረጉ እንደሚገኙ እና በቀጣይ ቀናትም ተጨማሪ ድጋፎች ለማድረግ በዝግጅት እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።

ከዚህ ቀደም የክለቡ ዋና አሰልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስ በግል ያሬድ ብርሀኑ እና ሀይማኖት ወርቁ ደግሞ ከሌሎች ተጫዋቾች ጋር በመሆን ድጋፍ ማድረጋቸው ይታወሳል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ