የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድኖች ለኮሮና ቫይረስ መከላከያ የሚውል ድጋፍ አድርገዋል

በዓለም ደረጃ ከፍተኛ ስጋት የሆነው የኮሮና ቫይረስ በሃገራችን እንዳይስፋፋ የሚደረገው ድጋፍ ቀጥሎ ዋሊያዎቹ እና ሉሲዎቹ በጋራ የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል።

ከሳምንቱ መጀመሪያ ቀናት ጀምሮ በተናጥል ገንዘብ ሲያሰባስቡ የነበሩት ሁለቱ ብሄራዊ ቡድኖች የሰበሰቡትን ገንዘብ በአንድ በማድረግ ዛሬ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢ/ር) አስረክበዋል።

በሁለቱም ቡድኖች የሚገኙ የአሰልጣኝ ቡድን አባላት፣ የተለያዩ ማህበራት፣ ደጋፊዎች፣ የቀድሞ እና የአሁን ተጨዋቾች ጨምሮ ከተለያዩ የስፖርት ቤተሰቡ የተሰበሰ 120000( አንድ መቶ ሃያ ሺ ) ብር እንደተሰበሰበ ተገልጿል። ቡድኖቹም ዛሬ ረፋድ 3:00 በመስተዳደሩ ቅጥር ግቢ በመገኘት በአሰልጣኞቻቸው እና በአምበሎቻቸው አማካኝነት ገንዘቡን አስረክበዋል።

በተያያዘ ዜናም በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ አስተባባሪነት መዋጮ ሲያደርጉ የነበሩት የኢትዮጵያ አሰልጣኞች ማኅበርም 125,000 (አንድ መቶ ሃያ አምስት ሺ) ብር በቦታው በመገኘት ለከተማ አስተዳደሩ ገቢ አድርገዋል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ