መቐለ 70 እንደርታ በአፍሪካ ውድድር ተሳትፎ ዙርያ ተቃውሞውን ገለፀ

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ኩባንያ የዘንድሮ የውድድር ዘመን በኮሮና ምክንያት እንዲሰረዝ ውሳኔ ማሳለፉን ተከትሎ የአፍሪካ ውድድር ተሳትፎ አለመኖር ውሳኔን እንደሚቃወም መቐለ 70 እንደርታ አስታውቋል።

ክለቡ ለሊግ ኩባንያው በላከው ባለ ሦስት ገፅ ደብዳቤ የሊጉን መቋረጥ እንደሚቀበለው የገለፀ ሲሆን የአፍሪካ ውድድር ተሳታፊዎች እንዳይኖሩ መወሰኑ ግን አግባብ አለመሆኑን አስቀምጧል። የአፍሪካ ውድድር አለመኖር ያለውን ተፅዕኖ የገለፀው ክለቡ ውሳኔ ለመወሰን የተሄደበትን አካሄድ “የክለባችንን አቋም ለመግለፅ እድል አልሰጠም” በማለት አሳታፊ አለመሆኑን ተቃውሟል። በተጨማሪም ክለቦች የሚደጎሙበት እና ወጪ የሚቀንሱበት መንገድ ለማመቻቸት ጥረት እንዲደረግ ጠይቋል። ለጠየቃቸው ጥያቄዎችም ፈጣን እና ተገቢ መልስ እንዲሰጠው በደብዳቤ ጠይቋል።

ደብዳቤው ይህን ይመስላል



👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ