በኢትዮጵያ ምድብ የምትገኘው አይቮሪኮስት ስብስቧን ይፋ አደረገች

በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ከኢትዮጵያ፣ ኒጀር እና ማዳጋስካር ጋር የተደለደለችው አይቮሪኮስት በቀጣይ ለምታደርጋቸው አራት ጨዋታዎች ስብስቧን ይፋ አደረገች።
ዝሆኖቹ በአዲሱ አሰልጣኝ ፓትሪስ ቡአሜሌ እየተመሩ ከቤልጅየም እና ጃፓን ጋር የወዳጅነት ጨዋታ የሚያደርጉ ሲሆን በመቀጠልም በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ከማዳጋስካር በደርሶ መልስ ይጫወታሉ። ለዚህ እንዲረዳቸውም ለሀያ ስድስት ተጫዋቾች ጥሪ አድርገዋል።

ጥሪ ከደረሳቸው መካአል ባለፉት ጨዋታዎች ከአሰልጣኙ ምርጫ ውጭ የነበረው አንጋፋው ጀርቪንሆ እና ባለፉት የማጣርያ ጨዋታዎች በጉዳት ምክንያት ያልተጫወተው ዊልፍሬድ ዛሃ ተካተዋል።

ምርጫው ይህንን ይመስላል:-

ግብ ጠባቂዎች

ሲልቪያን ግቦሆ (ቲፒ ማዜምቤ)፣ ኤሊዜ ታፔ (ሳንፔድሮ)፣ ኒኮላ ቴ (ጊዩማሬዥ)

ተከላካዮች

ኤሪክ ቤይሊ (ማን/ዩናይትድ)፣ ኢስማኤል ትራኦሬ (ኦንዠ)፣ ሲሞን ዴሊ (ብሩዥ)፣ ሲናሊ ዲዮማንዴ (ሊዮን)፣ ሰርጂ ኦሪዬ (ቶተንሀም)፣ ኦዲሎ ኮሶኑ (ብሩዥ)፣ ጄዲ አክፓ (ላዚዮ)፣ ማክስዌል ኮርኔ (ሊዮን)

አማካዮች

ጊስሌን ኮናን (ሬሚ)፣ ጂኦፍሬይ ዳይ (ሲዮን)፣ ሀቢብ ማይጋ (ሜትዝ)፣ ጂን ሚኬል ሴሪ (ፉልሀም)፣ ሞሐመድ ዶምቢያ (ፕራግ)፣ ፍራን ኬሲ (ሚላን)፣

አጥቂዎች

ኒኮላ ፔፔ (አርሰናል)፣ ማክስ ዣርዴል (ሲቫስፖር)፣ ጀርቪንሆ (ፓርማ)፣ ዊልፍሬድ ዛሃ (ፓላስ)፣ ክሪስቲያን ኩዋሜ (ፊዮሬንቲና)፣ ጁማ ሳይድ (አል ኩዌት)፣ ላጎ ጁንየር (ምዮርካ)፣ ጂን ኮዋሲ (ዉሀን ዛል)፣ ዊልፍሬድ ካኖን (ፒራሚድ)

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!