አዳማ ከተማ ከአሰልጣኙ ጋር በስምምነት ለመለያየት ወስኗል

አዳማ ከተማ ከአሰልጣኙ ጋር በስምምነት ለመለያየት ወስኗል

አዳማ ከተማ ቀሪ የአንድ ዓመት ውል ካላቸው አሰልጣኝ ጋር በስምምነት ለመለያየት መወሰኑን አረጋግጠናል።

በርካታ ወጣቶችን በትልቅ ደረጃ እንዲጫወቱ በማብቃት እና በሊጉ ጠንካራ ተፎካካሪ በመሆን የሚታወቀው አዳማ ከተማ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ከፋይናንስ እና ከሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ በመውረድ ስጋት ውስጥ በሆኖ ሊጉን የሚያጠናቅቅ ቡድን እየሆነ መጥቷል። በተጠናቀቀው የውድድር ዓመትም ፌዴሬሽኑ ሁሉም ቡድኖች ለ2018 በሊጉ ባሉበት እንዲቆዩ ባያደርግ ኖሮ አዳማ ከሊጉ ወርዶ እንደነበረ ይታወሳል።

ከሰሞኑ የክለቡ የበላይ አመራሮች ቡድኑን በቀጣይ በተሻለ ሁኔታ እንዲቀርብ ስብሰባዎችን እያደረጉ ሲሆን የአሰልጣኞች አባላትን ጠርተው ባደረጉት ግምገማ ከዋና አሰልጣኙ አብዲ ቡሊ ጋር አብሮ ላለመቀጠል ወስኗል። በዚህም መሠረት አሰልጣኝ አብዲ የአንድ ዓመት ቀሪ የውል ዘመን ያላቸው በመሆኑ በስምምነት ለመለያየት ንግግሮችን እያደረጉ ሲሆን በቀጣይ የወረቅት ጉዳዮች አልቀው እንደሚለያዩ ሶከር ኢትዮጵያ ያገኘችው መረጃ ያመላክታል።

አዳማ ከተማ ከአሰልጣኙ ጋር በስምምነት ከተለያየ በኋላ ፊቱን አዲስ አሰልጣኝ ወደ መቅጠር እንደሚያዞር ይጠበቃል።