አቤል ያለው ከግብጹ ክለብ ጋር በስምምነት ተለያይቷል

አቤል ያለው ከግብጹ ክለብ ጋር በስምምነት ተለያይቷል

ያለፉትን አንድ ዓመት ከስድስት ወራት በግብጹ ክለብ ቆይታ የነበረው አቤል ያለው በስምምነት መለያየቱ ተሰምቷል።

ባሳለፍነው ዓመት ከቅዱስ ጊዮርጊስ ከነበረው ጥሩ የውድድር ጅማሮ በኋላ ለሁለት ዓመት ከስድስት ወር ለመጫወት ከግብጹ ክለብ ‘Zed’ ጋር ስምምነት ማድረጉ ይታወሳል። ሆኖም ወደ ግብጽ ካመራ በኋላ እምብዛም የመጫወት እድል ያላገኘው አቤል አሁን በደረሰን መረጃ  ቀሪ የአንድ ዓመት ውል እያለው ከክለቡ ዜድ ጋር በስምምነት መለያየቱን ሰምተናል።

በወቅቱ በአዲስ አበባ ከፍተኛ ዲቪዚዮን ለሚጫወተው ለአቃቂ  ቃሊቲ በመጫወት የእግርኳስ ሕይወቱን የጀመረው ፈጣኑ አጥቂ ከዚህ ቀደም በሀረር ሲቲ፣ ደደቢት፣ ፋሲል ከነማ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ማገልገሉ ይታወሳል።

አቤል በቀጣይ በሀገር ውስጥ ወይም በሌላ የግብፅ ክለብ ይጫወታል የሚለውን በቀጣይ እንደሚያሳውቅ ይጠበቃል።