ቡናማዎቹ ሁለተኛ ፈራሚያቸውን ከወደ ናይጄሪያ የግላቸው አድርገዋል።
ባሳለፍነው የውድድር አመት ብርቱ ተፎካካሪ በመሆን ከሊጉ ሻምፒዮን ኢትዮጵያ መድን በመቀጠል ሁለተኛ ደረጃን ይዘው ያጠናቀቁት ቡናማዎቹ ለቀጣዩ የውድድር አመት ለተሻለ ተፎካካሪነት ይረዳቸው ዘንድ የናይጄሪያ ዜግነት ያለውን የመስመር አጥቂ አዳሙ አቡበከርን ወደ ስብስባቸው ቀላቅለዋል:: ከቀናት በፊት ዘላለም አባተን ከወላይታ ድቻ ያስፈረሙት ኢትዮጵያ ቡናዎች ሁለተኛ ፈራሚያቸውን ይፋ አድርገዋል።
የክለብ ጅማሮውን በ Haugesund ክለብ ያደረገው ይህ ተጫዋች በDesert star፣ Enyimba aba፣ Rivers united እና Plateau United መጫወት የቻለ ሲሆን ከክለብ ውጭ በብሔራዊ ቡድን መለያ ሀገሩ ናይጄሪያን ወክሎ በቻን ማጣሪያ ውድድር መሳተፍ ችሏል።
1 ሜትር ከ 69 የሚረዝመው ናይጄሪያዊው አጥቂ በቡናማዎች ቤት የሚያቆየውን የሁለት አመት ውል ተፈራርሟል።