አዲስ አዳጊው ሸገር ከተማ ወጣቱን የግራ መስመር ተከላካይ ለማስፈረም ተስማምቷል።
በተቋቋመ በአጭር ጊዜ ውስጥ በታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊ የሆነው ሸገር ከተማ ባለ ብዙ ልምዱን አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለን ዋና አሰልጣኝ አድርጎ ከሾመ በኋላ የነባር ተጫዋቾቸን ውል በማራዘም እና አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ስብስቡ በመቀላቀል ቡድኑን ለማጠናከር እየሰራ ይገኛል።
በዛሬው ዕለት ወጣቱን የግራ መስመር ተከላካይ ካሌብ በየነን ለማስፈረም በሁለቱ መካከል ከስምምነት መድረሳቸውን አውቀናል። ከሀዲያ ሆሳዕና ከታዳጊ ቡድን እስከ ዋናው ቡድን መጫወት የቻለው ካሌብ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በአርባምንጭ ከተማ በማሳለፍ አሁን መዳረሻውን ሸገር ከተማ ማድረጉን አውቀናል።