አዞዎቹ የግብ ጠባቂያቸውን ውል አራዝመዋል

አዞዎቹ የግብ ጠባቂያቸውን ውል አራዝመዋል

ቶጓዊው ግብ ጠባቂ ከአዞዎቹ ጋር ለመቀጠል ተስማምቷል።


ቀደም ብለው ከዋና አሰልጣኝ በረከት ደሙ ጋር ለመቀጠል ከስምምነት የደረሱት አርባ ምንጭ ከተማዎች አሁን ደግሞ ቶጓዊው ግብ ጠባቂ ኢድሪሳ ኦጎድጆ ለተጨማሪ ዓመት በቡድናቸው ለማቆየት ከስምምነት እንደደረሱ ታውቋል።

ባለፈው የውድድር ዓመት የቶጎውን ክለብ ኢንቴንቴ በመልቀቅ አዞዎችን ተቀላቅሎ በውድድር ዓመቱ በ18 ጨዋታዎች ተሰልፎ 1608′ ደቂቃዎችን ቡድኑን ያገለገለው ይህ ግብ ጠባቂ ከዚህ ቀደም ለፌይኖርድ ጋና፣ ጆሊባ እና ቫስኮ ደጋማን ጨምሮ ለበርከት ያሉ ክለቦች መጫወቱ ይታወሳል። አሁን ደግሞ ውሉን ለማራዘም ከስምምነት መድረሱን ተከትሎ በቀጣይ የውድድር ዓመት የአዞዎቹን ግብ የሚጠብቅ ይሆናል።