ኢትዮ ኤሌክትሪክ የአማካዩን  ውል አራዝሟል

ኢትዮ ኤሌክትሪክ የአማካዩን ውል አራዝሟል

አስቀድሞ ሁለት ነባር ተጫዋቾችን ማቆየት የቻሉት ኢትዮ ኤሌክትሪኮች የአማካኛቸውን ውል ለማራዘም መስማማታቸው እርግጥ ሆኗል።

አስቀድመው የአሸነፊ ጥሩነህ እና በፍቃዱ አስረሳህኝን ውል በማራዘም ወደ ዝውውሩ የገቡት ኢትዮ ኤሌትሪኮች በማስከተል የወሳኝ አማካዩን ሐብታሙ ሸዋለምን ለተጨማሪ ዓመት ከቡድኑ ጋር እንዲቆይ ውል ማረዘማቸው ታውቋል።

ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር የሊጉን ዋንጫ በማንሳት ከተለያየ በኋላ ኢትዮ ኤሌትሪክን ለአንድ ዓመት ለመጫወት የተቀላቀቀለው እና በ32 ጨዋታዎች ላይ ለቡድኑ ጥሩ አገልግሎት የሰጠው ሐብታሙ ሸዋለም ውሉን ያራመ ተጫዋች ነው። ሀብታሙ ከዚህ ቀደም በወልድያ ፣ በአዳማ ከተማ ፣ በስሑል ሽረ ተጫውቶ ማሳለፉ አይዘነጋም።