ቻምፒዮኖቹ የወሳኝ ተጫዋቻቸውን ውል አራዝመዋል

ቻምፒዮኖቹ የወሳኝ ተጫዋቻቸውን ውል አራዝመዋል

ባለፈው የውድድር ዓመት መድኖች የሊጉ ባለ ክብር እንዲሆኑ ጉልህ ድርሻ ያበረከተው ተከላካይ ከክለቡ ጋር ለመቀጠል ከስምምነት ደርሷል።

በሳምንቱ መጀመሪያ የግብ ጠባቀያቸው አቡበከር ኑራ እና የወጣቱ የመስመር ተከላካያቸውን በረከት ካሌብ ውል ለተጨማሪ ዓመታት ለማራዘም ከስምምነት የደረሱት ኢትዮጵያ መድኖች አሁን ደግሞ ባለፈው የውድድር ዓመት በ34 ጨዋታዎች በሙሉ በመሳተፍ ቡድኑ በሀያ ሁለቱ መረቡን እንዲያስከብር እና 15 ግቦች በማስተናገድ በሊጉ ዝቅተኛ የግብ መጠን ያስተናገደ ቡድን እንዲሆን ካስቻሉ ወሳኝ ተጫዋቾች አንዱ የሆነው ሁለገቡ ተጫዋች ንጋቱ ገብረስላሴን ለተጨማሪ ሁለት ዓመታት በቡድኑ ውስጥ ለማቆየት ከስምምነት ደርሰዋል።

በሊጉ ራሱን በጅማ አባ ጅፋር በመጫወት ያስተዋወቀው ንጋቱ በወላይታ ድቻን ቆይታ አድርጎ መድንን ከተቀላቀለ በኋላ በአመዛኙ በመሀል ተከላካይነትን በወጥነት ሲያገለግል መቆየቱ ይታወሳል።