አርባምንጭ ከተማ የተጫዋቾችን ውል ማራዘሙን ሲቀጥል አራት ተጫዋቾችንም ለተጨማሪ ዓመት ለማስቀጠል ተስማምቷል።
አሰልጣኝ በረከት ደሙን በአሰልጣኝነት ካስቀጠሉ በኋላ የተጫዋቾችን ውል በማራዘም የተጠመዱት አርባምንጭ ከተማዎች የቶጓዊውን ግብ ጠባቂ ኢድሪሱ ኦጎዶጆ ውል ማደሳቸውን ማሳወቃችን የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ የቀድሞው የወልቂጤ ከተማ ከዛም ደግሞ ረዘም ላሉ ዓመታት በአዞዎቹ ቤት ነግሦ የቡድኑ የከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ የሆነውን አህመድ ሁሴን ፣ የእግርኳስ ጅማሮውን በመተሐራ አድርጎ በመቀጥልም በድሬዳዋ ከተማ ፣ ጅማ አባጅፋር ፣ ሀዲያ ሆሳዕና እና ፋሲል ከነማ እንዲሁም ባለፈው ዓመት ደግሞ በአርባምንጭ ከተማ ያሳለፈው ይሁን እንዳሻውን ለሁለተኛ ዓመት ለማስቀጠል ውላቸውን ማደስ ችለዋል።
ቡድኑ በተጨማሪም የተከላካዮቹን አሸናፊ ፊዳ እና ብሩክ ባይሳን ውል ለተጨማሪ ዓመት አራዝሟል።