ወልዋሎዎች የቀድሞ ተጫዋቻቸውን ለማስፈረም ተስማምተዋል
ያለፉትን ሦስት ዓመታት ከነብሮቹ ጋር ቆይታ ያደረገው ፈጣኑ የመስመር ተጫዋች ሰመረ ሀፍታይ ከአምስት ዓመታት ቆይታ በኋላ ወደ አሳዳጊ ክለቡ ወልዋሎ ለመመለስ ከስምምነት ደርሷል።
ባለፈው የውድድር ዓመት በ27 ጨዋታዎች ተሰልፎ
1969′ ደቂቃዎች ቡድኑን ያገለገለው ወጣቱ የመስመር ተጫዋች ከነብሮቹ ጋር ያለውን ውል መጠናቀቁን ተከትሎ ስሙ ከበርካታ የሊጉ ክለቦች ጋር እየተያያዘ ቢቆይም በስተመጨረሻ ከአምስት ዓመታት በኋላ ወደ አሳዳጊ ክለቡ ለመመለስ ተስማምቷል።
ተጫዋቹ የእግር ኳስ ሂወቱን በወልዋሎ ጀምሮ በራያ ዓዘቦ፣ መቻል እንዲሁም ያለፉትን ሦስት ዓመታት በሀድያ ሆሳዕና መጫወት የቻለ ሲሆን አሁን ደግሞ በክረምቱ የዝውውር መስኮት የቢጫዎቹ ስድስተኛ ፈራሚ ሆኗል።