የመስመር ተከላካዩ ወደ አዳማ ከተማ አምርቷል

የመስመር ተከላካዩ ወደ አዳማ ከተማ አምርቷል

ባለብዙ ልምዱ የቀኝ መስመር ተከላካይ አዳማ ከተማን ለመቀላቀል ተስማምቷል።

ዘግይተውም ቢሆን ጠንከር ያሉ ዝውውሮችን በማድረግ ቡድናቸውን እያጠናከሩ የሚገኙት አዳማ ከተማዎች ከሰሞኑ ሀይደር ሸረፋን እና አቡበከር ሳኒን በማስፈረም ሲነቃቁ ከዚህ ቀደም ግብ ጠባቂው አላዛር ማርቆስ ፣ ብዙዐየሁ ሰይፉ ፣ መናፍ ዐወል እና ኢዮብ ማቲያስን የግላቸው ማድረጋቸው ይታወቃል። አሁን ደግሞ የቀኝ መስመር ተከላካዩን አብዱልከሪም መሐመድን ለማስፈረም መስማማታቸውን አውቀናል።

የቀድሞ የደቡብ ፓሊስ፣ ሐዋሳ ከተማ፣ ሲዳማ ቡና፣ ኢትዮጵያ ቡና፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ ፋሲል ከነማ እና ኢትዮጵያ መድን እንዲሁም ባለፈው አንድ ዓመት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ቆይታ የነበረው የመስመር ተከላካዩ የአንድ ዓመት ቀሪ ኮንትራት ቢኖረውም በስምምነት በመለያየት አሁን መዳረሻውን አዳማ ከተማ አድርጓል።