ምዓም አናብስት አማካዩን ለማስፈረም ተስማምተዋል

ምዓም አናብስት አማካዩን ለማስፈረም ተስማምተዋል

በፈረሰኞቹ ቤት ውሉን ለማራዘም ተስማምቶ የነበረው ተጫዋች ወደ መቐለ 70 እንደርታ ለማምራት ተስማምቷል።

ከቅዱስ ጊዮርጊስ ታዳጊ ቡድን ወጥቶ ባለፉት ውድድር ዓመታት በፈረሰኞቹ ቤት በዋናው ቡድን ደረጃ ስያገለግል የቆየው አማካዩ አብርሀም ጌታቸው ወደ መቐለ 70 እንደርታ ለማምራት ከስምምነት ደርሷል። ባሳለፍነው የውድድር ዓመት በ30 ጨዋታዎች ተሳትፎ 2358′ ደቂቃዎችን ቡድኑን ያገለገለው አማካዩ ከጥቂት ሳምንታት በፊት በእናት ክለቡ ለተጨማሪ ሁለት ዓመታት ውሉን ለማራዘም ቢስማማም በስተመጨረሻ ባልታወቀ ምክንያት ከቡድኑ ጋር ተለያይቶ ወደ መቐለ 70 እንደርታ ለማምራት ከስምምነት ደርሷል።

ቀደም ብለው የሶፎንያስ ሰይፈን ውል ለማራዘም ተስማምተው ኪቲካ ጅማን ለማስፈረም ከስምምነት የደረሱት ምዓም አናብስት አሁን ደግሞ አማካዩን ለማስፈረም መስማማታቸውን ተከትሎ ቡድኑን ለመቀላቀል ከስምምነት የደረሱ ተጫዋቾች ቁጥር አስራ አንድ ደርሷል።