አዳማ ከተማዎች በንቁ ተሳትፏቸው ቀጥለዋል

አዳማ ከተማዎች በንቁ ተሳትፏቸው ቀጥለዋል

ሁለገቡ ጋናዊ ወደ አዳማ ከተማ ለማምራት ከስምምነት ደርሷል።

በዝውውር መስኮቱ በርከት ያሉ ተጫዋቾች ለማስፈረም እንዲሁም የነባር ተጫዋቾች ውል ለማራዘም በመስማማት ቡድናቸውን በማጠናከር የሚገኙት በአሰልጣኝ ስዩም ከበደ የሚመሩት አዳማ ከተማዎች አሁን ደግሞ ሁለገቡን ጋናዊ ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰዋል፤ ቡድኑ ለመቀላቀል የተስማማው ደግሞ ጋናዊው ሚካኤል ሰፋ ነው።

በተከላካይ አማካይነት እና በመሃል ተከላካይ ቦታ ላይ መጫወት የሚችለው ይህ ጋናዊ ባለፈው የውድድር ዓመት በሀገሩ ክለብ አሻንቲ ኮቶኮ ቆይታ ያደረገ ሲሆን በእግርኳስ ሕይወቱም በህንዱ ‘BSS Sporting’፣  በጋቦን ክለቦች ፔሊካን እና ስታደ ሚጎቬን እንዲሁም ለሀገሩ ክለቦች መዳማ፣ ‘ፖርት ሲቲ’ እና ሌበሪቲ ፕሮፌሽናልስ መጫወት ችሏል። አሁን ደግሞ ወደ አዳማ ከተማ ለማምራት ከስምምነት መድረሱን ተከትሎ በክረምቱ የዝውውር መስኮት ክለቡን ለመቀላቀል የተስማማ የመጀመርያው የውጭ ዜግነት ያለው ተጫዋች ሆኗል። ተጫዋቹም በቀጣይ ቀናት ወደ ሀገር ቤት የሚገባ ይሆናል።