ሸገር ከተማን ለመቀላቀል ተስማምቶ የነበረው አማካይ ወደ ሌላው አዲስ አዳጊ አመራ።
የቅድም ውድድር ዝግጅታቸውን በባቱ ከተማ የጀመሩት እና በዝውውር መስኮቱ ዳዊት ተፈራ፣ በረከት ወልዴ ፣ ናትናኤል ሰለሞን፣ ሀቢብ ከማል እና ኢድሪሱ አብዱላሂን የግላቸው ያደርጉት ነገሌ አርሲዎች አሁን ደግሞ ባለፉት ዓመታት በኃይቆቹ ቆይታ የነበረው እና ከጥቂት ሳምንታት በፊት ወደ ሸገር ከተማ ለማምራት ከስምምነት ደርሶ የነበረው አብዱልበሲጥ ከማልን የግላቸው አድርገዋል።
ከኢትዮጵያ ቡና ታዳጊ ቡድን ከተገኘ በኋላ በአሳዳጊ ክለቡ ዋናው ቡድን፣ ደደቢት፣ ሰበታ ከተማ እንዲሁም ባለፉት ዓመት በሀዋሳ ከተማ ቆይታ ታታሪው አማካይ ከሀይቆቹ ጋር የነበረውን ውል አጠናቆ ወደ አዲስ አዳጊው ነገሌ አርሲ ማምራቱን ተከትሎ በክረምቱ የዝውውር መስኮት ወደ ክለቡ የተቀላቀለ ስድስተኛው ተጫዋች ሆኗል።
