የወቅቱ የብሔራዊ ቡድን አንበል እና ኮከብ ተጫዋች በቀጣይ ጨዋታዎች ዙርያ ሀሳቡን አጋርቷል

የወቅቱ የብሔራዊ ቡድን አንበል እና ኮከብ ተጫዋች በቀጣይ ጨዋታዎች ዙርያ ሀሳቡን አጋርቷል

👉”በእኛ አቋም እና ፊዚካል የጋራ የህብረት ሲሆን ለበለጠ ውጤት ይሻላል።”

👉”ምን እንኳን የማለፍ ዕድሉ ባይኖረንም የብሔራዊ ቡድን ማልያ ለብሶ መጫወት ትልቅ ክብር ነው።”

👉”ተጫዋች በግል፣ በቡድን ከሚያገኛቸው ስኬቶች በላይ ለብሔራዊ ቡድን መጫወት ትልቅ ስኬት ነው።”

አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ በቀጣይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዕየመሩ ከጊኒ ቢሳው እና ቡርኪና ፋሶ ጋር ለሚያደርጋቸው የመጨረሻ የምድብ ጨዋታዎች እና በተለያዮ ጉዳዮች ዙርያ ለተነሳባቸው ጥያቄዎች በዋናናነት የሰጡትን ምላሽ አስቀድመን ማጋራታችን ይታወሳል። አሁን ደግሞ አዲሱ የዋልያዎቹ አንበል ሀይደር ሸረፋ የሰጠውን ሀሳብ እንዲህ አቅርበናዋል።

ለጨዋታው የሰጡት ትኩረት

“ከፊት ለፊታችን ሁለት ጨዋታ አለ እኛ ደግሞ በሚገባ ተዘጋጅተናል። አሰልጣኙ በሚፈልገው መንገድ በመሄድ እስካለበት ድረስ እየገፋ እያሳየን ነው ያለው። እኛ ደግሞ ልምምድ ላይ ለመቀበል ፣ ለመተግበር ዝግጁ ነበርን። የወዳጅነት ጨዋታ ብናደርግ የተሻ ነበር። ተዘጋጅቶም ነበር ለማድረግ አልተሳካም እናተም እንደምታቁት ባልታሰበ
ምክንያት ማድረግ አልተቻለም። ከዓለም ዋንጫው ማጣርያ ውጭ እንደሆንን ይታወቃል። ለምሳሌ ያለፉትን ሁለት ጨዋታዎች ተሸንፈን መጥተናል። እዛ ላይ የነበሩ ድክመቶች ነበሩ። ጥሩ ጎኖችም ነበሩ ግን ከአሰልጣኞቻችን ጋር ተነጋግረን በምን መልኩ ብንጫወት ይሻላል በሚል ብዙ ነው ሲለፉ የነበረው። ምን እንኳን የማለፍ ዕድሉ ባይኖረንም የብሔራዊ ቡድን ማልያ ለብሶ መጫወት ትልቅ ክብር ነው። ብዙ ነገር ነው የምንወክለው ኃላፊነቱ ከባድ ነው ለማሸነፍ ነው የምንጫወተው። ስናሸንፍ ደረጃችን ይስተካከላል። ሌላው የክብር ጉዳይ ነው።”

አንበል ሆኖ ስለመመረጡ

“በመጀመርያ ለብሔራዊ ቡድን መመረጥ መለያ መልበስ የራሱ የተለየ ስሜት ይፈጥራል። የተጫዋች ትልቁ በግል በቡድን ከሚያገኛቸው ስኬቶች በላይ ለብሔራዊ ቡድን መጫወት ትልቅ ስኬት ነው። በተጨማሪ ደግሞ በአሰልጣኙ ተመርጦ አንበል መሆን ደግሞ የተለየ ስሜት አለው። ምን አልባት የተለያዮ ክለቦች አንበል ሆኜ ሰርቻለው። ብሔራዊ ቡድን መሆን በራሱ ትልቅ ሀላፊነት ነው፣ ትልቅ ደስታ ነው የሚፈጥረው። ግን ትልቅ የቤት ስራ አለብህ ሀላፊነቱ ቀላል አይደለም። ደስ ብሎኛል ኩራት ነው የሚሰማኝ።”

የሚያዋጠን የጨዋታ መንገድ በተመለከተ

“ጠለቅ ያለ ጥያቄ ነው። ለእኛ የሚያዋጣን የመጫወት መንገድ የቱ ነው ለተባለው። ትልቅ ጥያቄ ነው። እኔ በአጭር የምመልሰው አይደለም። ግን ከጋራ ከህብረት ጋር የተያያዘ ነገር እኛን ያዋጣናል ብዬ አስባለው። በማጥቃቱም በመከላከሉም እንደ አሰልጣኙ ፍላጎት ይለያያል በእርግጥግን በእኛ አቋም እና ፊዚካል የጋራ የህብረት ሲሆን ለበለጠ ውጤት ይሻላል።” ብዬ አስባለው ብሏል።